ስለ እያንዳንዱ መጽሐፍ ይዘት ያንቡይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው። መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። መጽሐፉ ቀላልና ግልጽ በሆነ የአጻጻፍ ስልት ቢጻፍም “ያለ መምህር መማሪያ” ለመሆን ከበድ ሊል ይችላል ብየ አምናለሁ። በመሆኑም “አውደ ጥናትን መጎብኘት አይዘንጉ። ከዚህ መጽሐፍ ላቅ ያለ ዕውቀት ያላችሁ አንባብያን ለወጣንያንና ለማዕከላውያን1 የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው። ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው። ሌላው ተማሪዎች ለጥናት የበለጠ እንዲተጉ በማሰብ በመጽሐፉ ውስጥ የቀረቡት ጥያቄዎች እየተመለስን መጽሐፉን እያነበብን የምንመልሳቸው ናቸው እንጅ መልሳቸው አልተሰጠም።
|
✨ Welcome to Ge’ez Wisdom ! Discover the language of angels — Geʽez — and grow in your faith through ancient knowledge and modern learning tools. 🔗 Explore the Pages: 🔤 Ge’ez Alphabet Lessons 📖 Word of the Day 📚 Bible Study Series 🛠️ Study Tools ▶️ YouTube Channel 🛎️ Bookmark this blog and visit often — new content is always on the way! 🙏 May your study be blessed. ✍️ Start your journey with the Ge’ez Alphabet
Comments
Post a Comment